የወያኔ ፌደራል ፖሊስ አዛዥ የVOA ጋዜጠኛን መተው እንደሚያስሩት የተናገሩበት ቃለ ምልልስ

በ VOA ጋዜጠኛ ሰለሞን ክፍሌ (Washington DC) እና በቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ሳጅን ዘመድኩን መካከል የተደረገ ቃለ መጠይቅ፡
ጋዜጠኛ ሰለሞን፡ በሙስሊሙ ማህበረሰብ ያነጣጠረ የቤት ለቤት ፍተሻ እየተካሄደ ነው ስለተባለ፤ ሁኔታው ለማጣራት ነው የደወልኩት
ሳጅን ዘመድኩን፡ እሺ
ጋዜጠኛ ሰለሞን፡ ትክክል ነው? ፍተሻ እያካሄዳቹ ነው?
ሳጅን ዘመድኩን፡ ይሄን ኣላቅም ጌታዬ፤ ማነው እንደዛ ብሎ ያለህ?
ጋዜጠኛ ሰለሞን፡ የጥቃቱ ሰለባ የሆኑት ነን የሚሉ ሰዎች፤ ሙስሊሞቹ ናቸው፤ እዛ አካባቢ የሚኖሩ
ሳጅን ዘመድኩን፡ እንግዲህ እንደዛ ካሉ እነሱን ይጠቁዋ
ጋዜጠኛ ሰለሞን፡ እነሱ ያሉትን ለእርሶ ልገልጽሎት እችላለሁ
ሳጅን ዘመድኩን፡ እሺ ምንድ ነው ያሉት?
ጋዜጠኛ ሰለሞን፡ ፍተሻው የሚካሄደው በፖሊሶች ነው፤ ይገቡና ያለ ፍርድ ቤት ማዘዣ ያስፈራሩናል፡ ንብረትም ይወስዳሉ በተለይ የሚያተኩሩት በቁርዓን እና በሞባይል ፎን ላይ ነው እንዲህ እንዲህ ይላሉ፡፡ እና ይህንን ለማጣራት ነው እርሶ ጋር የደወልኩት
ሳጅን ዘመድኩን፡ እንግዲህ እነሱ ያሉት ሰዎች ቢጠይቁ አይሻልም እኔ ማውቀው ነገር የለም
ጋዜጠኛ ሰለሞን፡ እሱማ ጠየቅኩ፤ ነገርኮት እኮ የሚሉትን
ሳጅን ዘመድኩን፡ በቃ እንግዲህ ማውቀው ነገር የለም አባቴ
ጋዜጠኛ ሰለሞን፡ ይህንን ያሉኝን እጠቅሳለሁ ሳጅን ዘመድኩን ማን ልበል? የቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ኖት?
ሳጅን ዘመድኩን፡ አው እነደዛ ነኝ፤ አው
ጋዜጠኛ ሰለሞን፡ ሳጅን ዘመድኩን ማን ልበል?
ሳጅን ዘመድኩን፡ ይቅርታ አባቴ እንደዚ ዓይነት ስልክ ማንንም ማናገር አልፈልግም ልዘጋው ነው ካሁን በኃላ ቢደውሉ ባድራሻዎት እይዞታለሁ ይህንን እንዲያውቁ ካሁን በኃላ በዚህ ስልክ ቢደውሉ ያሉበት ቦታ መጥቼ እወስዶታለሁ፡፡አሁን ማለት ነው፡፡
ጋዜጠኛ ሰለሞን፡ እኔ እኮ ያለሁት ዋሺንግተን ነው
ሳጅን ዘመድኩን፡ ዋሺንግተን አይደለም መንግስተ ሰማያት ይኑሩ፤ እኔ ምንም ሚያገባኝ ነገር የለም፤ ግን አመጣዎታለሁ፡፡ እንዲያውቁ፡፡
ጋዜጠኛ ሰለሞን፡ መጥተው ይወስዱኛል?
(ስልኩ ተቓረጠ)